Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደሴ ከተማ በሚገኘው የሰይድ ያሲን የንግድ ማእከል እና ድርጅቶች በአሸባሪው ህወሃት መዘረፋቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በደሴ ከተማ በሚገኘው የሰይድ ያሲን የንግድ ማእከል ውስጥ ይሰሩ የነበሩ 113 ድርጅቶች በአሸባሪው ቡድን መዘረፋቸው ተገለጸ።

አሸባሪው ቡድን ከዘረፈው የሕዝብ ሀብት በተጨማሪ በህንጻው ውስጥ የነበረውን ሀብት በመሰባበር እና በተለያዩ መልኮች ከጥቅም ውጭ አድርጓል።

የአሸባሪው ቡድን የጥፋት ክንድ ካረፈባቸው እና በንግድ ማእከሉ ከነበሩ ድርጅቶች መካከል ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ ካፍቴርያዎች፣ የሞባይል እና ልዩ ልዩ ሱቆች፣ የሴቶች የውበት ሳሎን፣ የትምህርት እና የጤና ተቋማት እና መሰል የሕዝብ መገልገያዎች ይገኙበታል።

አሸባሪው ቡድን ካወደማቸው መካከል በህንጻው ውስጥ ከፍ ባለ ደረጃ የአልጋ አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጁ በነበሩ 42 የመኝታ ክፍሎች ውስጥ የነበሩ ሙሉ ቁሳቁሶች መዘረፋቸውን እና ተሰባብረው መውደማቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው ቅኝት ተመልክቷል።

የአልጋዎቹ እና ለአልጋ አገልግሎቱ እየተዘጋጁ በነበረበት ወቅት የተዘረፉት እና የወደሙት ቁሳቁሶች ግምታዊ ዋጋም 25 ሚሊዮን ብር እንደሚደርስ ተነግሯል።

በማእከሉ በአጠቃላይ የደረሰው ግምታዊ ዋጋቸው እየተጠና ይገኛል፡፡

በለይኩን አለም

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version