አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሐረርጌ ዞን 18 የሸኔ የሽብር ቡድን አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡
የሸኔ የሽብር ቡድን አባላቱ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በሚኤሶ ወረዳ የሽብር ተግባር ሊፈጽሙ ሲንቀሳቀሱ በአካባቢው የጸጥታና የኅብረተሰብ ተሳትፎ እስከ ጉቢ ቦርዶዴ ወረዳ በመከታተል እርምጃ እንደተወሰደባቸው የሚኤሶ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ሳጅን ኦላና አህመዲን ገልጸዋል፡፡
የምዕራብ ሐረርጌ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ኢደቻ በበኩላቸው ÷ ከሚኤሶ ወረዳ እስከ ጉምቢ ቦርዶዴ በተካሄደ ኦፕሬሽን 18 የሸኔ ቡድን አባላት ላይ እርምጃ መውሰድ ሲቻል 4 አባላቶቻቸው ደግሞ ከያዙት 11 የክላሽንኮቭ ጠብመንጃ እና 14 ሙሉ የጥይት ካርታ ጋር ተማርከዋል ብለዋል፡፡
በቀጣይም ኅብረተሰቡ መረጃ የመስጠት ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና ቡድኑ እስከሚወገድ ድረስ ከጸጥታ አካላቱ ጎን እንዲቆም የምዕራብ ሐረርጌ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

