Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ሊመልስ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ሊመልስ ነው
 
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ሊመልስ እና አገልግሎት ሊያስጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡
 
አየር መንገዱ የቦይንግ 737-ማክስ አውሮፕላኖች ዳግም ወደ ስራ ለመመለስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁንና የመጀመሪያ በረራውን በፈረንጆቹ የካቲት 1 ቀን 2022 እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም÷ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት መስጠት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
አየር መንገዱ 737-ማክስ አውሮፕላኖችን ዳግም ወደ ስራ ሲመልስ የተለያዩ ሀገራት የአቪዬሽን ቁጥጥር ተቋማት ለአውሮፕላኑ የበረራ ፈቃድ ከሰጡ በኋላ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
 
አየር መንገዱ የቦይንግ 737- ማክስ አውሮፕልንን ወደ ስራ ለመመለስ እና አገልግሎት በማስጀመሩ ከመጨረሻዎቹ አየር መንገዶች ተርታ ለመሰለፍ በገባው ቃል መሰረት የዲዛይን ማሻሻያ ስራውንና ከ20 ወራት በላይ የፈጀውን ጥብቅ የማረጋገጫ ሂደት ሲከታተል እንደቆየ ተገልጿል።
 
በዲዛይን ማሻሻያውና በታለፈው ማረጋገጫ ሂደትን ተከትሎም አብራሪዎች፣ መሐንዲሶች፣ የአውሮፕላኑ ቴክኒሻኖችና የበረራ ባለሙያዎች በአውሮፕላኑ ደህንነት ላይ እንደሚተማመኑ ተጠቅሷል፡፡
 
በሚቀጥለው አንድ ወር ውስጥ ለተጓዦች ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚያሳውቅ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version