Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አገሪቱ ያሉባትን ትላልቅ ተግዳሮቶች ለመፍታት አካታች አገራዊ ምክክር በጣም አስፈላጊ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገሪቱ ያሉባትን ትላልቅ ተግዳሮቶች ለመፍታት አካታች አገራዊ ምክክር በጣም አስፈላጊ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለፁ።
 
አቶ አደም አካታች አገራዊ ምክክርን አስፈላጊ የሚያደርጉ በርካታ ተግዳሮቶች አሉ ብለዋል።
 
በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የለም ያሉት ኃላፊው፥ በህገ መንግስቱ፣ ሰንደቅ ዓላማ፣ አገር ግንባታ ላይ እና በሌሎችም መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የለም ነው ያሉት።
 
አገራችን እስካሁን ከግጭትና ከጦርነት አዙሪት መውጣት እንዳልቻለችና እንደ አገር ዴሞክራሲን ከመትከልና ከማጽናት አኳያ ሰፊ ክፍተት እንዳለ አንስተዋል።
 
የጋራ ማንነትንና ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን እንደ አገር ማረጋገጥ እንዳልተቻለም ነው አቶ አደም ያመለከቱት።
 
እነዚህን ትላልቅ ተግዳሮቶች ከመፍታት አኳያ አካታች አገራዊ ምክክር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ተብሎ እንደሚታመን ገልፀዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version