Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብሄራዊ ኮሚቴው “በታላቁ ጉዞ ወደ ሃገር ቤት” የዳያስፖራ አቀባበል መርሃ ግብሩን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ኮሚቴው “በታላቁ ጉዞ ወደ ሃገር ቤት” የዳያስፖራ አቀባበል መርሃ ግብሩን ይፋ አድርጓል፡፡
የብሄራዊ ኮሚቴው የኦፕሬሽናል ዘርፍ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የተቀናጀ ዝግጅት መደረጉን አረጋግጠዋል።
ዳያስፖራዎች ሀገር ችግር በገጠማት ጊዜ በሚችሉት ነገር ሁሉ አኩሪ ተግባር ሲያከናውኑ እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትር ዲኤታዋ የአሁንም ጥሪ ሀገራቸውንና ወገናቸውን በብዙ መልክ እንዲያግዙ በማለም የተሰናዳ ጥሪ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በመድረኩም የመርሃ ግብሩ ዝርዝር የተጠቀሰ ሲሆን÷ በዚህም ከታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ይፋዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም በወዳጅነት ፓርክ ይደረጋል ተብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን መጎብኘት፣ ለመከላከያ ሰራዊት አባል ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረግ፣ የአረንጓዴ አሻራን ማሳረፍ፣ ዳያስፖራውን በመልሶ ግንባታና ማቋቋም ላይ የሚያሳትፍ ዝግጅትና የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴን የሚያግዝ ፎረም በዝግጅቱ ተካቷል።
ከታህሳስ 25 ቀን2014 ዓ.ም ጀምሮ ዳያስፖራው በህወሓት የሽብር ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎችና የተፈናቀሉ ዜጎችን የሚጎበኝበትና ድጋፍ የሚያደርጉበት መርሃግብር መካተቱን የብሄራዊ ኮሚቴው አስታውቋል።
የመስህብ ስፍራዎችን ማዕከል ያደረጉ በርካታ ዝግጅቶችን ጨምሮ ገናን በላሊበላና ጥምቀትን በጎንደር ከዳያስፖራው ጋር ለማሳለፍ መርሃግብር ተዘጋጅቷል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዲኤታዋ ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው÷ ዳያስፖራው በመስህብ ስፍራዎች ላይ በአግልግሎት አሰጣጥ ላይ ያልተፈለገ ችግር እንዳይገጥመው በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።
በቆንጂት ዘውዴ፤ ተጨማሪ መረጃ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version