Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፋር ክልል ካቢኔ አባላት የተሰጣቸውን አቅጣጫ እና ተልዕኮ አፈፃፀም ገመገሙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፋር ክልል ካቢኔ አባላት ተሰጠው የነበሩ አቅጣጫዎች እና ተልዕኮዎችን አፈፃፀም በዛሬው ዕለት ገምግመዋል፡፡
 
መድረኩ ከሳምንት በፊት በሰመራ ከተማ በተካሄደው የከፍተኛ አመራርና መካከለኛ አመራር መድረክ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችና የተሰጠው ተልዕኮ አፈጻጸምን መገምገም ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
 
ከጦርነት ወደ ሰላም ጎዳና በሚል በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ አዋል አርባ ተገኝተዋል፡፡
 
በመድረኩ የፓርቲ ሥራ እቅድ አፈፃፀም ፣ የአመራር ልየታ ፣ በጦርነቱ የደረሰው ውድመትና ኪሳራ እና የመከላከያ ምልመላ በተመለከተ ተሰጥቶ የነበረው ተልዕኮና አቅጣጫ በጥልቀት ተገምግሟል።
 
በአምስቱ አጀንዳ ላይ አመራሮች ፣ አባላት ፣ ምሁራን ፣ ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የነበረው ተሳትፎ ምን ይመስል እንደ ነበር መገምገሙንም ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አባላቱ በአምስቱ አጀንዳ ክንውንና አፈጻጸም ግምገማ የነበሩ ድክመቶችን እናጥንካሬዎችን ከለዩ በኋላ ÷የተሰራው ሥራ ውጤታማና የተሰካ እንደ ነበረ አመላክተዋል፡፡
 
በቀጣይ አገራዊ እና ክልላዊ ሁኔታንና ሌሎች አቅጣጫዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ መተግበር እንዳ ለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version