አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል የጥፋት ተግባር ጉዳት ደርሶበት የነበረውን የአለውሃ ድልድይ የጥገና ስራ ተጀምሯል።
የጥገናው ስራ ከ8 እስከ 10 ቀናት ውስጥ ተጠናቅቆ ለትራፊክ ክፍት እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡
የድልድዩ ፕሮጀክት ሳይት መሃንዲስ ኢንጂነር ዮሐንስ አያሌው ለኢፕድ እንደተናገሩት÷ የተሰበረውን ድልድይ ወደስራ ለማስገባት የብረት ድልድይ ማስቀመጥ የሚያስችለው የግንባታ ስራ ተጠናቋል፡፡
ከነገ ጀምሮ ባሉት ቀናት ደግሞ ድልድዩን የመገጣጠምና የማጠናቀቅ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል፡፡
እንደ ኢንጂነር ዮሐንስ ገለጻ÷ የብረት ድልድዩ አጠቃላይ ርዝመቱ 54 ነጥብ 86 ሜትር ሲሆን፥ የድልድዩ መቀመጫ (ፓድ) ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡
የብረት ድልድዩን የመገጣጠም ስራ ከ5 እስከ 7 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን÷ ከ8 እስከ 10 ቀናት ውስጥ የድልድይ ሥራው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ይሆናል ተብሏል፡፡
የሚሰራው የብረት ድልድይ እስከ 600 ኩንታል ወይም 60 ቶን ድረስ መሸከም የሚችል አቅም መሆኑን ገልጸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

