Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቱርክ የኢትዮጵያውያን አንድነት እና ትብብር ማህበር ለተፈናቃዮች 28 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ የኢትዮጵያውያን አንድነት እና ትብብር ማህበር ከመንግስት የተደረገውን የድጋፍ ጥሪ በመቀበል በጦርነት ለተፈናቀሉ እና ለተቋማት መልሶ ግንባታ የሚውል 28 ሺህ ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
የማህበሩ አባላት ወደ ሀገር ቤት በሚሄዱበት ወቅት ገንዘቡን ለሚመለከተው አካል እንደሚያስረክቡ በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃመድ ተናግረዋል፡፡
 
ማህበሩ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ በሚቀጥልበትና ዳያስፖራው በሀገራዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት በሚሳተፍባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት መደረጉንም ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በቱርክ የኢትዮጵያውያን አንድነት እና ትብብር ማህበር በፈረንጆቹ 2020 ታህሳስ ወር ላይ ነው የተመሰረተው፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version