Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአሸባሪው ቡድን የወደሙ ተቋማትን ከሕዝብ ጋር የማቋቋም ስራ ይሰራል – ዶክተር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ከሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ምክክር አድርገዋል።

አሸባሪው ቡድን በአማራ ላይ በፈጸመው ወረራ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ በተካሄደው ትግል ኢትዮጵያውያን ነፃነታቸውን እና ክብራቸውን በመስዋእትነት ማስጠበቅ መቻላቸውንም አንስተዋል።

በተደረገው ትግልም የዋግ ሚሊሻ ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጉንም ርእሰ መሥተዳድሩ ገልጸዋል።

የሃይማኖት አባቶችም ለማኅበረሰቡ ያደረጉት አስተዋጽኦ ጊዜ የማይሽረው አባታዊ ተግባር ነው ብለዋል።

የውስጥ አንድነትን አጠናክሮ ጠላትን መታገል እንደሚገባ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ይህን ለማድረግም መንግሥት የጸጥታ መዋቅሩን እንደሚያደራጅ አውስተዋል።

ወጣቶችም የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እና የአማራ ልዩ ኃይልን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የዋግ ሕዝብ ጠላትን ፊት ለፊት የታገለ ጀግና መሆኑንም ርእሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

ነዋሪዎች በበኩላቸው መንግሥት የውኃ፣ የመብራት፣ የባንክ እና መሰል ተቋማትን ችግሮች በአጭር ጊዜ በመፍታት አገልግሎት እንዲያስጀምር መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version