አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ንግድ ለሰላምና ለዘላቂ የኢትዮጵያ ልማት” የንግዱ ማህበረሰብ የምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር እና በኢንሼቲቭ አፍሪካ ትብብር የተዘጋጀው የምክክር መድረክ የኢትዮጵያ የሰላም ፖሊሲና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና ተግዳሮቶች እና ዕድሎች ላይ ከተለያዩ ከንግድ የዘርፍ ማህበራትና ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ከተውጣጡ የንግድ ማህበረሰብ አካላት ጋር ምክክር ተደርጓል፡፡
የንግዱ ማህበረሰብ ከትርፋማነቱ ባሻገር በሰላምና ብሔራዊ መግባባት ላይ የጎላ ሚና መጫወት እንደሚገባው የተጠቆመ ሲሆን፥ ለግጭት መንስኤ የሆኑትን ስራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነት፣ የኢኮኖሚ አሻጥርና መሰል ተግባራትን ከምንጊዜውም በላይ መከላከል እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአ የንግድ ተቋማት የአገር ምሰሶዎች ናቸው የሰላም ዕሳቤዎችን በስራቸው ውስጥ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
አያይዘውም ÷ የንግድ ተቋማት የሀገርና የማህበረሰብን ጥቅም ባስቀደመ መልኩ በመስራት የስራ ዕድሎችን በመፍጠር የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና በመጋራት ሰላምና መረጋጋትን ሊያሰፍኑ ይገባል በማለት ገልፀዋል፡፡
የንግዱ ዘርፍ መብቱን የሚጠይቅ፣ ግዴታውን ያለአስታዋሽ የሚወጣ እንዲሁም በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃላፊነቱን የሚወጣ እንዲሆን ማስቻል የኢትዮጵያ የሰላም ፖሊሲ ዋነኛ ዓላማዎች እንደሆኑ መገለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

