Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለወደሙ የጤና ተቋማት ድጋፍ የሚውል 50 ኮንቴነር የህክምና ቁሳቁስ ወደ ኢትዮጵያ የማጓጓዝ ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ለወደሙ የጤና ተቋማት ድጋፍ የሚውል 50 ኮንቴነር የህክምና ቁሳቁስ ከካናዳ ወደ ኢትዮጵያ የማጓጓዝ እንቅስቃሴ መጀመሩን በካናዳ የኢመርጀንሲ ህክምና የግሎባል ኤድ ኢትዮጵያ መስራች ዶክተር ጌታቸው ደመም ገለጹ።
በካናዳ የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የአገራቸውን ጉዳይ በንቃት እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸው÷ በኢትዮጵያ ያጋጠመውን ወቅታዊ ችግር ተከትሎ ለሀገራቸው አስፈላጊውን ምላሽ እየሰጡ እንደሚገኙም ነው ያነሱት።
 
የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ እየተሰባሰበ እንደሚገኝ፣ ከፕሮጀክት ኪዩር ጋር በመሆን 50 ኮንቴነር የሚሆን የህክምና ቁሳቁስ መሰብሰቡን እና ወደ ሀገር ቤት ለመላክ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ተናግረዋል።
 
እስካሁን ባለው ሂደት 5 ኮንቴነር የህክምና ቁሳቁስ ወደ ሀገር ቤት መላኩንም አስረድተዋል።
 
ከድጋፉ ባሻገር ከካናዳ የመጡ የህክምና ቡድን አባላት በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ሙያዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል።
 
በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚኖር ዳያስፖራ ለአገሩ የሚያደርገውን ድጋፍ ይበልጥ እንዲያጠናክር ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
Exit mobile version