Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮን እና ወገል ጤና ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አገኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች የደረሱ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ውድመትና ብልሽቶችን በመጠገን እና መልሶ በመገንባት የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ስራው ቀጥሏል፡፡

በዚህም በሰሜን ወሎ ዞን የምትገኘው ኮን ከተማ እና በደቡብ ወሎ ዞን የምትገኘው ወገል ጤና ከተማ የተቋረጠባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል መልሰው ማግኘት ችለዋል፡፡

ነፃ የወጡ አካባቢዎችን ዳግም ኃይል መልሰው እንዲያገኙ ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ ያሉ የተቋሙ የስራ መሪዎች በተሸከርካሪ፣ በዲስትሪቢዩሽን ዕቃዎች እና በመሳሰሉት ላይ የአቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ድጋፍና ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙ ተነስቷል፡፡

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች በበኩላቸው ÷ ከምንጊዜውም በበለጠ እልህ አስጨራሽና ቁጭት የተሞላበት ጥረት በማድረግ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱ ላይ የጥገና እና መልሶ የመገንባት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

አሸባሪው ህወሃት ወራሪ ቡድን በመካከለኛ እና ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ አስተላለፊ መስመሮች፣ ትራንስፎርመሮች ፣ ቆጣሪዎች እና ሌሎች የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ግብዓቶች ላይ ካደረሰው ጉዳት ባሻገር በደንበኞች አገልግሎት መስጫ ቢሮዎች፣ በቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች፣ በዕቃ ማከማቻ መጋዝኖች፣ በዎርክ ሾፓችና ጋራዦች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version