አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2014(ኤፍ ቢሲ) በበጋ የመስኖ ልማት ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ስንዴን በመስኖ ለማልማት ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለስ መኮንን እንደገለጹት፥ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ በበጋ ወቅት ስንዴን በመስኖ በማምረት ተሰፋ ሰጪ ለውጦች የተመዘገቡ በመሆኑ በቀጣይ ይህን አጠናክረን በማስቀጠል በያዝነው የምርት ዘመን ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የመስኖ ስንዴ በማልማት ከ16 ሚሊየን ኩንታል በላይ ለማምረት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
እስከ ታህሳስ አጋማሽ ባለው ጊዜ ከ250 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በስንዴ ዘር ለመሸፈን ተችሏል፡፡
ግቡን ለማሳካት የግብዓትና ቴክኖሎጂዎች አቅርቦት ድጋፍ የተደረገ ከመሆኑም በላይ የከፍተኛ አመራችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን በየቦታው ተገኝተው ድጋፍ እንዲያደርጉ ተደርጎል ብለዋል፡፡
ከዚሁ ጎን ለጎን ግን በመደበኛው የመስኖ ስራ በሁሉም ክልሎች በሚባል ደረጃ ያሉትን የመሬትና የውሃ አማራጮችን በአግባቡ በመለየት ወደ ተጨባጭ ተግባር በመግባት በአንደኛ ዙር የመስኖ ስራ ግማሽ ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት ታቅዶ ከ300 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣በስራስር እና ሌሎች በሰብሎች የመሸፈን ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
የመኸር እርሻ በተሰበሰበበት ቦታዎች ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፥ በህግ ማስከበሩ ዘመቻው ላይ የተሳተፉ አርሶአደሮችን ሰብል ከመሰብስብ ጎን ለጎን በወረራ ተይዘው የነበሩት አካባቢዎች ነፃ በመውጣታቸው በነዚህ አካባቢ የበልግ አብቃይና የመስኖ ስራ አመቺ የሆኑ አካባቢዎች ጭምር ተለይቶ እቅድ በማውጣት ቶሎ ወደ ስራ በመግባት የምርት መቀነስ ለመተካት በቁጭት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

