Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ ይመረጣሉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ እንደሚመረጡና ሹመታቸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚጸድቅ የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ፥ የኮሚሽነሮች ጥቆማ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያሳትፍ ሲሆን ፥ ከተጠቆሙት 14 እጩዎች መካከል 11 ተመልምለው በአፈ ጉባኤው አቅራቢነት በምክር ቤቱ የሚሾሙበት አሰራር ተዘርግቷል ብለዋል።
ኮሚሽነሮቹ በምክር ቤቱ ከተሰየሙበት እለት ጀምሮ ለ3 ዓመታት የሚቆይ የስራ ጊዜ እንደሚኖራቸው ተጠቁሞ፥ እንደ አስፈላጊነቱ ቆይታቸው ሊራዘም እንደሚችልም ተገልጿል።
በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ስለ ድርድር የሚገልጽ ምንም አይነት ይዘት አለመካተቱን ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።
የአዋጁ ዋና አላማ እስካሁን መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸውና የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያካተተ ውይይት በማድረግ ችግሮችን መፍታት እንደሆነ አመላክተዋል።
የሚቋቋመው ኮሚሽን ከምክክር መድረኮቹ የሚያገኘውን ምክረ ሀሳብ በመቀመር ተግባራዊ እንዲደረጉ እንደሚሰራ አንስተው ፥ ምክር ቤቱን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት ወስደው እንደሚያስፈጽሙና ለስኬታማነቱም ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት እንደሚዘረጋ ሰብሳቢዋ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁ ይታወቃል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version