አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)”የህልውና ዘመቻውን በመደገፍ የተፈጥሮ ሀብት ማልማት ስራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል”በሚል መሪ ቃል በባህር ዳር ከተማ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ ተካሄደ።
መድረኩ በክልሉ ግብርና ቢሮ የተዘጋጀ ሲሆን÷ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በአማራ ክልል ያሉ አመራሮች በርካታ ተግባራት የሚጠብቋቸው እንደሆነ ይታወቃል፤ በዚህም የተጀመረው የንቅናቄ መድረክ በጎ ጅምር ነው ብለዋል ።
በክልሉ በርካታ ማህበረሰብ አርሶ አደር በመሆኑ መሬቱን ለም ለማድረግ ፣ ውሃው እንዳይደርቅ ለመከላከልና ምርታማ እንዲሆን ለማድረግ የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅ ተገቢ በመሆኑ ስራው በዘመቻ መጀመሩ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ክልሉ ያለው ከፍተኛ ሀብት መሬት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይሄን መሬት መንከባከብ ደግሞ ግድ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ መፍጠር እና የባለቤትነት ስሜት እንዲኖረው መስራትም እንደሚጠበቅም ነው የተናገሩት።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሀይለማርያም ከፍያለው በበኩላቸው÷ ክልሉ በብዛት የሚተዳደረው በግብርናው ዘርፍ በመሆኑ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰዋል።
ለዚህ ደግሞ ተፈጥሮ ሀብትን በተገቢው መንገድ ማልማትና መጠበቅ እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በስንታየሁ አራጌ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

