Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ ለሚሳተፉ በጣሊያን ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሽኝት መርሃ ግብር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዳያስፖራው ያቀረቡትን ግብዣ ተቀብለው በጋራ ወደ አገር ቤት ለመግባት በዝግጅት ላይ ለሚገኙ በጣሊያን ሮም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሽኝት መርሃ ግብር ተደረገ፡፡
በመርሃ ግብሩ በጣሊያን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ ÷ ኢትዮጵያ በገንዘብ፣ በአይነት እና በሰልፍ የሚደግፍ እና የምዕራባውያንን ተፅዕኖ በተለያየ መንገድ በድፍረት የሚታገል ጀግና የዳያስፖራ ኮሚዩኒቲ እንዳላት እና ይህም ካለባት ጊዜያዊ ችግር ቶሎ ለመላቀቅ ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው አብራርተዋል።
በተጨማሪም “እናንተ ዘማች ናችሁ፤ ዘማች ደግሞ አገርና ወገኑን ከጥፋት ለመታደግ ነው የሚዘምተው ስለሆነም ከምትይዟቸውና ከምትገዟቸው ቁሳቁስ ጀምሮ በሚኖራችሁ ቆይታ እና በምታደርጉት እንቅስቃሴ ለአገርና ወገን ድጋፍ በሚያስገኝ ሁኔታ ላይ መሆን አለበት” ብለዋል።
የዳያስፖራ አባላቱ በበኩላቸው÷ መንግስት ባቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ አገር ቤት በመግባት የደረሰውን ጥፋት በአካል በመመልከት በመልሶ ግንባታው የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሄዱ ገልፀዋል፡፡
ዛሬም ሆነ ወደ ፊት አገር እና ወገን በሚፈልጓቸው በማንኛቸውም ጊዜ የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version