አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ የፀረ አፓርታይድ ስርዓት ታጋይና ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።
የቀብር ስርዓቱ በኬፕ ታውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ የተፈጸመ ሲሆን፥ የሊቀ ጳጰሱን ፎቶ በመያዝ ብዛት ያላቸዉ ሰዎች በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሃገሪቱ በከፍተኛ መጠን መሰራጨቱን ተከትሎ ለቀብሩ የመጡ ሰዎችን የኮቪድ ህግጋቶችን መሰረት ባደረገ መልኩ የቀብር ስርዓቱ መፈጸሙን ቲ አር ቲ ዎርልድ በዘገባው አመላክቷል፡፡
ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ስርዓት እንድትላቀቅ ሲታግሉ የነበሩት ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ ህልፈተ ህይወታቸውን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካውያን ሳምንቱን ሙሉ ሀዘናቸውን ሲገልፁ ሰንብተዋል፡፡
ለጋስ፣ ሩህሩህ እና ታጋይ የሚባሉት ዴዝሞንድ ቱቱ በ90 አመታቸዉ ባለፈዉ እሁድ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ላደረጉት መልካም ተግባር የአለም ሃገራት መሪዎች ምስጋና ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

