አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ (ሹርባ) በጎንደር ከተማ አቀባበል ተደረገለት።
ከፍተኛ የፌደራል፣ የክልል እና የከተማ አመራሮች የአፄ ቴዎድሮስን ቁንዳላ አቀባበል አድርገዋል።
የአፄ ቴዎድሮስ ሹርባን የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ ተረክበዋል።
ጥር 6 በሚከበረው የንጉሱ ልደት እና የጥምቀት በዓል መርሃ ግብር አካል እንደሚሆንም ተገልጿል።
በጎንደር ከተማ በሚገኘው ራስ ግንብ ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚጎበኝ የከተማው ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ቻላቸው ዳኛው ተናግረዋል።
ከንጉሱ ቁንዳላ (ሹርባ) በተጨማሪ ይገለገሉባቸው የነበሩ ጦር እና ጋሻዎች ከፀሎት መጽሃፋቸው ጋር በውስት ዛሬ ጎንደር ገብተዋል።
በክብረወሰን ኑሩ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!