Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚደረገውን መልሶ ማቋቋም ሁሉም ዜጋ ሊከውነው እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገር ውስጥ እና በውጪ የሚኖሩ የላስታ እና ላልይበላ ተወላጆችና ወዳጆች 6 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጪ በማሰባሰብ ለአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
የቅዱስ ላልይበላ ጊዜያዊ የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ÷አካባቢው በአሸባሪው ቡድን በወረራ ተይዞ በቆየበት ጊዜያት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ አስቸኳይ መድሃኒቶችንና የምግብ ነክ ድጋፎችን በሁለት ዙር የጋማ ከብቶችን በመጠቀም ማድረሱን ገልጿል፡፡
 
በዚህም በጊዜው ሆስፒታሎ እና ሌሎች የጤና ተቋማት በመውደማቸው እና አገልግሎት በማቋረጣቸው ማህበረሰቡ ለካፋ ችግር ተጋልጦ በነበረበት ሰዓት ኮሚቴው ከአካባቢው የሃይማኖት አባቶች እና ሽማግሌዎች ጋር በመተባበር መድሃኒቶችን ማድረሱን የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደሳለ ምትኩ ገልጸዋል።
 
ላልይበላ እና አካባቢው ከወረራ ነጻ ከሆነ በኋላ የላስታ እና ቅዱስ ላልይበላ አስቸኳይ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የምግብ አይነቶችን ግዢ በመፈጸም ለ3ኛ ዙር ለማህበረሰቡ አድርሷል ነው ያሉት።
 
በሶስተኛው ዙር የተደረገው ድጋፍ ከ300 ኩንታል በላይ ዱቄት ፣4 ሺህ 500 ሊትር ዘይት ፣ 20 ኩንታል በርበሬ እና ሌሎች ቁሶችን ያካተተ ነው፡፡
 
ኮሚቴው በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርገውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የገለጸው፡፡
 
በሽብር ቡድኑ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ በማቋቋሙ ረገድ መንግስት ከሚያደርገው በተጨማሪ ሁሉም ዜጋ ሊረባረብ እንደሚገባም አቶ ደሳለኝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በፍሬህይወት ሰፊዉ
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version