አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በኢንሸስትመንት መስክ የሚሰማሩ ዳያስፖራዎችና ባለሃብቶች ለማስተናገድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩ አቡሃይ ÷ የአገርን ጥሪ ተቀብለው ወደ ጎንደር ከተማ የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ በሁሉም መስክ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የጥምቀት በዓልን በጎንደር ለመታደም የሚመጡ ዲያስፖራዎች በከተማዋ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲሰማሩ ሁኔታዎችን የሚያመቻች የኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል።
ከተማዋ ሰፊ የመልማት አቅም አላት ያሉት ምክትል ከንቲባው ÷ በቡድንና በተናጠል በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ ዳያስፖራዎች ቅድሚያ ይሰጣል ብለዋል።
ቅድሚያ ካሳ ከፍለው ወደ ማልማት ለሚገቡ ባለሃብቶች የኢንዱስትሪ መንደር የተዘጋጀ መሆኑንም ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
በጎንደር ከተማ በኢንቨስትመንት መስክ ተሰማርተው ለማልማት ለሚፈልጉ ዲያስፖራዎች የሚለማ ቦታ እየተዘጋጀ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ከንቲባው ÷ ከተማዋ ሰላም መሆኗ ተመራጭ ያደርጋታል ብለዋል።
በየትኛውም ዘርፍ ጎንደር ከተማ መዋለ ንዋያቸውን ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ ከተማ አስተዳደሩ በቂ ዝግጅት እያደረግኩ ነው ብሏል።
የጥምቀት በዓልን ተከትሎ የኢንቨስትመንት ፎረም በከተማዋ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።
በምናለ አየነው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

