Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባለፉት 24 ሰዓታት 2 ሺህ 140 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 2 ሺህ 140 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ÷ለ6 ሺህ 176 ዜጎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሺህ 140 ዜጎች ቫይረሱ እንዳለባቸው መረጋገጡን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
 
ባለፉት 24 ሰዓታት 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸውንም ነው ሚኒስትሯ የገለጹት
 
በሌላ በኩል 1ሺህ 490 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን÷442 ዜጎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
Exit mobile version