Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ቡድን በወልዲያ ከተማ ከዘረፈው እና ካወደመው ንብረት በተጨማሪ ነዋሪዎችም ላይ የሥነ-ልቦና ቀውስ አድርሷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወልዲያ ከተማ ከ22 በላይ የመንግስት ተቋማትን ያወደመው እና የዘረፈው አሸባሪው የህውሓት ቡድን ነዋሪዎችም ላይ የሥነ-ልቦና ቀውስ ማድረሱ ተገልጿል።
አሸባሪው የህውሓት ቡድን በከተማዋ ሴቶችን ደፍሯል የሰው ሕይወትም አጥፍቷል፡፡
የከተማዋን ነፃ መውጣት ተከትሎም ነዋሪዎቿ ወደቀደመ እንቅስቃሴያቸው ተመልሰዋል፡፡
አካባቢውን ለቆ የሄደው የኅብረተሰብ ክፍልም እየተመለሰ ሲሆን፥ ሆቴል ቤቶች እና የንግድ ተቋማትም ወደ ስራ ገብተዋል፡፡
ነዋሪዎቹ ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ መረዳት ያለባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡
መንግስት በኅብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ወደ ሥራ ለመለወጥ አቅጣጫ አስቀምጦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተመልክቷል፡፡
የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ፥ የውስጥና የውጪ ባንዳዎችን በመለየት ሠላማችንን እንጠብቅ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share
Exit mobile version