Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአርብ ገበያ-ሰከላ-ቲሊሊ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርብ ገበያ-ሰከላ-ቲሊሊ ክፍል ሁለት የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የግንባታ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ።

62 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገዱ ግንባታው ከእቅዱ ጋር ተጣጥሞ በመልካም የስራ ክንውን ላይ እንደሚገኝ በመስክ ጉብኝት ወቅት መመልከቱን አስተዳደሩ አስታውቋል።

በእስካሁኑ የሥራ እንቅስቃሴ የቅየሳ ስራ፣ የአፈር ቆረጣና ሙሌት፣ የውሃ መተላለፊያ/መፋሰሻ ቱቦዎች ሥራ፣ የሰብ ቤዝ ሥራዎችን ጨምሮ በርካታ የስትራክቸር ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብሏል፡፡

የአራት ድልድይ ግንባታ በፕሮጀክቱ የተካተተ ሲሆን፥ ለዚህም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጀምረዋል።

ለአሰፋልት ንጣፍ ስራው የሚያገለግሉ አስፈላጊ ማሽነሪዎች በሙሉ ተተክለው ከወዲሁ ግብአት ማምረት መጀመራቸውን አመልክቷል።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ መንገዱ የሰከላ እና ቲሊሊ ወረዳዎችን እንዲሁም አቻኖ እና ጉንዲልን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎችን በቅርበት ያገናኛል፡፡

የመንገድ ግንባታውን በ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር  በሆነ ወጪ እያከናወነ የሚገኘው ዲ ኤም ሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ አገር በቀል ኩባንያ ነው። ግንባታው የሚጠይቀው ሙሉ ወጪም በኢትየጵያ መንግስት መሸፈኑን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version