አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ 110 ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች አበረከተ፡፡
ክፍለ ከተማው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በህገ ወጥ ተይዘው የነበሩ ቤቶችን በማስለቀቅ ነው በኑሮ ዝቀተኛ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በስጦታ ያበረከተው።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አባወይ ዮሀንስ÷በከተማዋ የሚስተዋለውን የቤት ችግር ለመፍታት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች 103 የመኖሪያ ቤቶች እና ሰባት የንግድ ቤቶች መተላለፋቸውን ተናግረዋል፡፡
ቤቶቹ 15 በመቶ ለአቅመ ደካሞች፣ 27 በመቶ ለወጣቶች፣ 40 በመቶ ለሴቶች፣ 6 በመቶ ለአካል ጉዳተኞች እንዲሁም 10 በመቶ ለሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች መተላለፋቸው ተገልጿል፡፡
በቅድስት ብርሀኑ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

