Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ውድመት የደረሰባቸው 3 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነዉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በሽብር ቡድኑ ህወሓት ከፍትኛ ውድመት የደረሰባቸውን ሶስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እስከ የካቲት 30 ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ከትናንት ምሽቱ ፋና ዜና መጽሄት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ በአጠቃላይ ከ4 ሺህ 300 በላይ ትምህርት ቤቶች በሽብር ቡድኑ ህወሓት ጥቃት የተፈጸመባቸው ሲሆን ÷ ከእነዚህ ውስጥ 190ዎቹ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን አብራርተዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች ተፈናቅለው የሚሄዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ያረፉት በትምህርት ቤቶች በመሆኑም ችግሩን ሰፊ አድርጎታል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው÷ትምህርት ቤቶቹን በሚቻለው አቅም ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግርዋል።

በዚህ መሰረትም የባንክ ሂሳብ በማዘጋጀትም ከዳያስፖራዎች ጋር መድርኮችን ለማዘጋጀትም እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ችግሩ ያልተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን ጉዳት ከደረሰባቸው ጋር በማቀናጀት እንዲረዳዱ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በዚህ አሰራርም ሶስቱ የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ተጠግነው እስከ የካቲት 30 ስራ ይጀምራሉ ተብሎ እቅድ ተይዟል ነው ያሉት።

የትምህርት ተቋማቱን የመጠገን ስራ የመንግስት ብቻ ሊሆን ስለማይችል አጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰቡ በሃብት ማሰባሰብ ስራው እንዲሳተፍ እና የንግዱ ማህበረሰብም የበኩሉን እንዲወጣ ዶክተር ሳሙኤል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በትዕግስት ስለሺ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version