አዲስ አበባ፣ታህሳስ 27፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ከ10ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በአለም ከተማ የአርበኞች ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዘመናዊ ቤተመጻህፍት ለመገንባት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
የመሰረት ድንጋዩን ያሰቀመጡት የጤና ሚኒስትር ዴኤታና የአካባቢው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካይ ዶ/ር አየለ ተሾመ እንደገለጹት÷ትምህርት ቤቱ ያለበትን ችግር ለመቅረፍ የአካባቢው ተወላጆችን በማስተባበር ነው ዘመናዊ ቤተ መጻህፍት ለመገንባት ስራ የተጀመረው።
ግንባታው ከ10 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከአንድ ሺህ በላይ ተማሪዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ ቤተመፃህፍት ነው ያሉት ዶክተር አየለ÷በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ እንሰራለን ብለዋል፡፡
ለግንባታውም በርካታ ግለሰቦች ቃል መግባታቸውን ነው የገለጹት ።
የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና መምህራን በበኩላቸው÷ትውልድን ለመገንባት ትኩረት ሰጥተው የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና የአካባቢው ተወላጆች የጀመሩት ስራ የተማሪዎችና የመምህራንን የረጅም ጊዜ ችግር የሚፈታና አርአያነት ያለው ተግባር ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

