አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙት እስታይሽ፣ አሁን ተገኝ፣ ሀሙሲትና ቦያ ከተሞች ወራሪው የትግራይ ቡድን ወደ አካባቢው ዘልቆ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አግኝተዋል፡፡
በአካባቢው የደረሰው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ በክልሉ በሚገኙ የአገልግሎቱ ሰራተኞች እረፍት አልባ ጥረት እና እልህ አስጨራሽ ስራ የመካከለኛ እና ዝቅተና መስመሮች ጥገና ተጠናቋል፡፡
ይህን ተከትሎም ከተሞቹ ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው ዕለት ዳግም ማግኘት መቻላቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

