አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አዲስ የተሾሙ የአስር አገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ አዲስ የተሾሙትን የጣሊያን አምባሳደር አጎስቶ ፓሌስ፣ የማላዊ አምባሳደር ሻርልስ ፒተር ምሶሳ፣ የፍልስቴም አምባሳደር ፋርስ አልቁብ፣ የጊኔ ቢሶ አምባሳደር ኢብራሂማ ሳኖ፣ የቡርኪናፋሶ አምባሳደር ኦሊቪያ ሮአምባ፣ የታንዛኒያ አምባሳደር ኢኖሰንት ኡጂን ሺሆ፣ የኩባ አምባሳደር ጆርግ ፌርናንዶ ለፈብሬ ኒኮላ፣ የተባበሩት የአረብ ሊግ አምባሳደር ወሊድ ሀስመድ ሺልታግብ፣ የብሩንዲ አምባሳደር ዊሊ ኒያሚትዌ እና የሴኔጋል አምባሳደር ሞሀመድ ላሚን ቲአው የሹመት ደብዳቤ ነው የተቀበሉት፡፡
ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ከየአገራቱ ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አጽንኦት መስጠታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

