አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልእክት÷ ለእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆን የተመኙ ሲሆን÷ በዓሉ ሲከበር የተቸገሩ ወገኖቻችን እና ለሀገር ክብር በግዳጅ ላይ ያሉ የጀግናው መከላከያ ሰራዊት አባላትን ቤተሰብ ደጀን መሆናችንን በማስመስከር መሆን አለበት ብለዋል።
አቶ ሙስጠፌ በመልእክታቸው፥ በክልሉ ፈታኝ እና ከባድ የሆነ የድርቅ አደጋ የተጋረጠበት እና ያንንም ለመቀልበስ የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር ሌት ተቀን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ በትላንትናው ዕለት የክልሉ መንግስት ካቢኔ እና የመንግስት ኃላፊዎች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለዚሁ የድርቅ አደጋ ምላሽ እንዲሆን መስጠታቸውን ማስታወሳቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ይህ በዓል ሲከበርም በድርቅ አደጋ ህይወታቸው አደጋ ውስጥ የገቡ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎችንም ያሰበ መሆን አለበት ያሉት አቶ ሙስጠፌ፥ መንግስት ከሚያደርገው ያላሰለሰ ጥረት በተጨማሪ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎችና ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ማድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

