አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ ፥ አዘዞ ቀበሮ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአሸባሪው ቡድን ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፕ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ጋር የልደት በዓልን አክብረዋል።
ከንቲባው ለተፈናቃዮች ማዕድ ያጋሩ ሲሆን ፥ የከተማው ህዝብ ከተፈናቀሉ ወገኖች ጎን በመቆም ድጋፍ ሲያደርግላቸው እንደቆየም ተናግረዋል።
በዓልን ብቻ ሳይሆን ሁሌም ከእናንተ ጋር የተለያዩ ድጋፎችን እያደረግን ወደ ቀያችሁ እስክትመለሱ ድረስ በተጠናከረ መንገድ እገዛችን ይቀጥላል ብለዋል።
ከንቲባው በፀዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመገኝት የቆሰሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም እንደሚጎበኙ ታውቋል።
በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ ሰራተኞች፥ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ሀብት በማሰባሰብ ከተፈናቃዮች ጋር በዓሉን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተዋል።
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የጎንደር ኤፍኤም 105.1 ሰራተኞች በደባርቅና በጎንደር ግምቱ 500ሺህ ብር የሚገመት ቁሳቁስ ለተፈናቃዮች ለበዓል ድጋፍ ማድረጋቸውን የጣቢያው አስተባባሪ ወይዘሮ እመቤት ሁነኛው ገልፀዋል።
በምናለ አየነው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!