አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ላይ የተፋሰስ ልማት ስራ ሊከናወን መሆኑ ተገለጸ፡፡
መርሃ ግብሩ ጥር 6 በአስር ዞኖች እና በ56 ወረዳዎች ይጀመራል የተባለ ሲሆን፥ የተፋሰስ ልማት ሥራው አርብቶ አደሮችን፣ አርሶ አደሮችን እና መላውን የኅብረተሰብ ክፍልና አመራር ባሳተፈ መልኩ ለ60 ቀናት እንደሚከናወን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አበራ ወርቁ ተናግረዋል፡፡
ሀላፊው 6 ሺህ 448 የተፋሰስ ልማት የሚከናወንባቸው ቦታዎች መለየታቸውንም ገልጸዋል።
መርሃ ግብሩን በተቀናጀ መልኩ ለመምራት 1 ሺህ 141 የአሰልጣኞች ስልጠና የወሰዱ ባለሙያዎች ከህብረተሰቡ ጋር እንደሚሰሩም ተገልጿል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተሰራው የደን ማልማት ሥራ ለግብርናው ምርታማነት ለውጥ አምጥቷልም ተብሏል።
በመጪው ክረምት በኦሮሚያ ክልል 4 ነጥብ 4 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል የታቀደ ሲሆን፥ ይህንኑ ለማሳካት እስካሁን 6 ሺህ 22 የችግኝ ዘር መዘጋጀቱም ተመላክቷል።
በ2013 ከተተከሉት 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኞች መካከል 3 ነጥብ 8 ቢሊየኑ መጽደቁን ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

