አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጋር በተያያዘ በወዳጅነት ፓርክ አደባባይ ባዛር፣ ኤግዚቢሽንና የሙዚቃ ኮንሰርት የመክፈቻ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ነሲሴ ጫሊ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር መሃመድ እድሪስ እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡
በዝግጅቱ የቆዳ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የአበባ፣ የቅመማ ቅመም፣ የብረታብረት እና የተለያዩ የአገር ውስጥ ምርቶች ለገበያ ቀርበዋል፡፡
የመርሀ ግብሩ ዋና ዓላማ የገበያ ትስስር መፍጠር ሲሆን ፥ ዳያስፖራው በሚመለስበት ወቅት ምርቶቹን ገዝቶ ውጭ ላለው የዓለም ህብረተሰብ እንዲያስተዋውቅ ነውም ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያን ምርቶች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በብዛት እና በጥራት ለማምረት ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ነው መርሀ ግብሩን ያዘጋጁት፡፡
ኤግዚቢሽኑ በይፋ ተከፍቶ ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

