Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዳያስፖራው እያመጣቸው ያሉ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች በጥንቃቄ እንዲቀመጡ ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው ወደ አገር ቤት እያመጣቸው ያሉ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች በተገቢው ጥንቃቄ ለአገልግሎት ምቹ ሆነው እንዲቀመጡ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጥሪ ተቀብለው በርካታ ዳያስፖራዎች ወደ አገር ቤት እየገቡ ሲሆን ፥ ወደ አገር ቤት ከገቡትም መካከል ብዙዎቹ በአሸባሪው ህወሃት ለወደሙ የጤና ተቋማት መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን ይዘው መምጣታቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከጤና ሚኒስቴርና ከመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ጋር በጋራ በመሆን መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶቹ በተገቢው ጥንቃቄ እንዲከማቹ እየሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

በባለስልጣኑ የማዕከላዊ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ረዳት ዳይሬክተር ህሊና ገዛኸኝ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ዳያስፖራው ወደ አገር ቤት እያመጣቸው ያሉ መድሃኒቶችና የህክምን ቁሳቁሶች በተገቢው ጥንቃቄ ተቀምጠው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው፡፡
መድሃኒቶቹና የህክምና ቁሳቁሶቹ ወደ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ተልከው በጤና ሚኒስቴር በኩል ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ተደራሽ እንደሚሆኑም አስታውቀዋል።

ባለስልጣኑ ዳያስፖራው የጤናውን ዘርፍ በግብዓት ለመደገፍ እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version