አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የህዝብ ቁጥር ዕድገት ምጣኔንና የተፈጥሮ ሃብቶች ልማትን በማጣጣም የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ ገለፁ።
የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ለክልሉ ካቢኔ አባላትና ለካቢኔ መስሪያ ቤቶች የልማት ዕቅድ ባለሙያዎች በስነ ህዝብ ዙሪያ ስልጠና ሠጥቷል።
በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፥ ስነ- ህዝብ በሃገር ልማት ማዕቀፍ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ሰፊ የልማት አጀንዳ ነው ያሉ ሲሆን፥ መንግስት የህዝብ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በግንባር ቀደምትነት ካወጣቸው ፖሊሲዎች አንዱ የስነ-ህዝብ ፖሊሲ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በክልሉ ስነ-ህዝባዊ ትሩፋትን እውን ለማድረግም የዕድሜ አወቃቀር ለውጥን ማፋጠንና ትሩፋቱን በማሳካት በኩል የማይተካ ሚና ባላቸው በጤና፣ በትምህርት፣ የስራ እድልና መልካም አስተዳደር ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevisio

