አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ አለም ለከተሞች ዘላቂ ልማት የሚሰራው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋም ዩ ኤን ሀቢታት የአፍሪካ ቢሮ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ኦማር ሲላ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮጵያ መንግስት እና ድርጅቱ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በትብብር እና በቅንጅት መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በተለይም በዘላቂ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ በከተማ ልማት፣ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መልሶ ማቋቋም፣ በንጽህና አጠባበቅ ፕሮጀክቶች እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ተጠባባቂ ዳይሬክተር ኦማር ሲላ፥ ዩ ኤን ሀቢታት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከፈረንጆቹ 1998 ጀምሮ ጠንካራ ግንኙነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው፥ እስካሁንም በኢትዮጵያ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች 10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገንዘብ ማፍሰሱን ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር መለስ አለም በበኩላቸው፥አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት ባደረሰው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ድርጅቱ በሽብር ቡድኑ የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቀም የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍ ጥሪ ማቅረባቸውንም በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

