አዲስ አበባ፣ ጥር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትና ኤምባሲዎች የሚካፈሉበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር ያዘጋጀው መድረክ እየተካሄደ ነው።
መድረኩ በፓን አፍሪካኒዝም ላይ እየመከረ ነው።
በመድረኩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ዳያስፖራዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶችና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።
አፍሪካዊነት ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፥ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በሚፃረር መልኩ ከውጪና ከውስጥ የተለያዩ ጫናዎች መደረጋቸውን አንስተዋል።
ጫናው በአንድነቷ የማትደራደረውን ኢትዮጵያ ቢፈታተንም አላሸነፋትም ነው ያሉት።
በፈተናዋ ወቅት በርካታ አፍሪካዊያን ከጎኗ መቆማቸውን የ”በቃ” (Nomore) ዘመቻም ድጋፍ እንደተቸረው ጠቁመዋል።
አፍሪካ በዳግም ቅኝ ግዛት ፍላጎቶች እጇ እንዳይጠመዘዝ ተቋማዊ አሰራሮች እንዲደራጁ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላትም ነው የገለጹት።
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት እንድትወከልም መስራት እንደሚገባ አክለዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ እንድሪስ በበኩላቸው፥ አዲሱን የምዕራባዊያንን የዳግም ቅኝ ግዛት ፍላጎት ለማክሸፍ አፍሪካዊ ዳያስፖራዎች በጋራ መስራት አለባቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎችም በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ ከአፍሪካዊያን ጋር እንቆማለን ነው ያሉት።
በመድረኩ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአፍሪካና እስያ ጉዳዮች ተመራማሪው ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ፥ በሽብርተኝነት መከላከል፣ ሰላምና ደህንነት፣ በሰብዓዊ መብትና መሰል አጀንዳዎች ሰበብ ጣልቃ የመግባት የምዕራባዊያን የቅኝ ግዛት ፍላጎቶች መኖራቸውን ይሄንን ለማክሸፍም አፍሪካዊያን በትብብር መስራት እንዳለባቸው ነው ያነሱት።
ዳያስፖራዎች በተለይም የአፍሪካን ድምፅ በማሰማትና ኢኮኖሚያዊ አቅምን በማሳደግ መሥራት አለባቸው ብለዋል።
ሥራዎችን ከዘመቻ ይልቅ ወደ ተደራጀ ተቋማዊ አሰራር ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
አፈወርቅ እያዩና በርናባስ ተስፋዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

+2
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share