አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ በሣምንት ውስጥ ሁለተኛውን የባላስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏ ተገልጿል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ከስድስት ቀናት በፊት የሃይፐርሶኒክ ባላስቲክ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ ካስወነጨፈች በኋላ ነው ሁለተኛውን በዛሬው እለት ማስወንጨፏ የተነገረው፡፡
የደቡብ ኮሪያ ጥምር ጦር አዛዦች ፥ ሰሜን ኮሪያ ሁለተኛውን የባላስቲክ ሚሳኤል መሬት ላይ ከተጠመደ ማስወንጨፊያዋ ወደ ምስራቃዊ ባህር ዳርቻዋ ሳታስወነጭፍ እንዳልቀረ ገልጸዋል፡፡
ሁለተኛው የሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ደቡብ ኮሪያን ማሰቆጣቱ የተገለጸ ሲሆን፥ የደቡብ ኮሪያ እና የአሜሪካ ጦር ሃይሎች የሀገሪቱን የሚሳኤል ሙከራ በቅርበት እየተከታተሉት መሆኑን ቲ አር ቲ ወርልድ በዘገባው አስታውቋል፡፡
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እና የመከላከያ ሚኒስቴር ሰሜን ኮሪያ ያሰወንጨፈችው የባላስቲክ ሚሳኤል መሆኑን የገለጹ ሲሆን፥ ዝርዝር መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ እንደገለጹት፥ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በጃፓን ዙሪያ ያሉትን መርከቦች እና አውሮፕላኖች ደኅንነት እየፈተሹ ሲሆን፥ ሰሜን ኮሪያን ተደጋጋሚ ሚሳኤል ማሰወንጨፍ ተክትሎ እስካሁን የደረሰ ጉዳት የለም፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ሰሜን ኮሪያ ቀደም ሲል ለወሰደችው የሚሳኤል እርምጃ እየተወያየ ባለበት ሀገሪቱ ሚሳኤሎችን መተኮሷን መቀጠሏ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፉሚዮ ኪሺዳ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

0
People reached
0
Engagements
–
Distribution score
Boost post
Like
Comment
Share