Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብረት ምርትን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ለመተካት የሶስት ዓመት የፕሮጀክት ጊዜ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብረት ምርትን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ለመተካት የሶስት ዓመት የፕሮጀክት ጊዜ መቀመጡን በማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ዑማ፥ ከብረት አምራቾች ፣ ከሙያተኞች ፣ ከኢኮኖሚ ባለሙያዎች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተውጣጥቶ ከተቋቋመ ሀገራዊ የብረት ምርት ስትሪግ ኮሚቴ ጋር ሥራው የደረሰበትን ሂደት ገምግመዋል፡፡

ይህን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፥ ከውጪ የምናስገባቸውን የማዕድን ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እየሰራን ያለነው ስራ በፍጥነት በተግባር እየተገለፀ ይገኛል ብለዋል።

በቀጣይም የመጀመሪያ የቅድመ አዋጪነት ጥናት እና የፋብሪካ ግንባታ ቦታ መረጣ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ተስማምተናል ነው ያሉት።

የብረት ምርትን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ለመተካትም የሶስት ዓመት የፕሮጀክት ጊዜ ተቀምጧል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ፕሮጀክቱን የሚያስተባበር “ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት” በማዕድን ሚኒስቴር አስተባባሪነት መዋቀሩንም አስታቀዋል፡፡

ስራውም በመንግስት ፣በሀገር ውስጥ ባለሀብቶችና በውጪ ባለሀብቶች በጋራ የሚከናወን ይሆናል ብለዋል ኢንጂነር ታከለ ዑማ ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version