አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራችን ውስብስብ ችግሮች ቢገጥሟትም ዕምቅ አቅም እና ትልቅ ተስፋ ያላት በመሆኑ በተለይ ከተሞች ላይ ዕድሎችን ተጠቅሞ ለወጣቶች ሥራ መፍጠር እንደሚገባ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ንጉሡ ጥላሁን ገለጹ፡፡
በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በ11 ከተሞች 70 ሺህ ወጣቶችን አስልጥኖ የሥራ ዕድል ለማመቻቸት ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ለሙከራ ትግበራ በአዲስ አበባ ከተማ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሁለት ወረዳዎች የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ያላገኙ ወጣቶችን አሰልጥኖ የሥራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ በማመቻቸት ሥራ የማስያዝ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ነው የተባለው፡፡
ወጣቶችን አሰልጥኖ ለሥራ ልምምድ ወደ ተለያዩ የግል ተቋማት ሲላኩ ሊደረግላቸው በሚገባ ድጋፍ እና የሥራ ፈጠራ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን የሚያስገነዝብ ውይይት ተካሂዷል፡፡
መንግስት ለሥራ ፈጠራ ምቹ ሁኔታ የመፍጠር እና የሚስተዋሉ ውስብስብ ችግሮችን የመፍታት ኃላፊነት አለበት ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው÷ ባለሀብቶች እና አጋር አካላት በዋናነት ወጣቱን ማዕከል አድርገው ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል፡፡
የሥራ አጥነት ችግር ጎልቶ በሚታይባቸው ከተሞች ላይ ትኩረት ማድረግ ተገቢ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ነው የተናገሩት፡፡
ለውይይት እንደመነሻ የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም አጠቃላይ ዓላማ እና የተቋማት ሚና እንዲሁም በተግባር ላይ ልምምድ ወቅት የሴት ወጣቶች ተሳትፎን በተመለከተ ገለፃ መደረጉን
ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በየዓመቱ ለ10 ሺህ 500 የከተማዋ ወጣቶች በአምራቹ ዘርፍ ሥራ ለማመቻቸት እየተሠራ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ÷ በአዲስ አበባ ለሚገኙ 49 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ባለሀብቶችና አጋር አካላት ለሰጡት ምላሽ አመስግነዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

