Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመሆን ለቅዱስ ላሊበላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር ለቅዱስ ላሊበላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ2 ሚሊየን 800 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ፥ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተፈጠረው ግጭት አሸባሪው ቡድን ባደረሠው ዝርፊያና ውድመት የተጎዱ ተቋማትን ለመደገፍ እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማጠዝ የተሰጠ ነው ብለዋል።
ድጋፉ ተጎጂ ወገኖች የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ የጤና ተቋማትን ለማቋቋም ያለመም መሆኑን አቶ ተመስገን ገልፀዋል።
የተጎዱ የጤና ማዕከላት መልሶ ማቋቋም ከሁሉም ተቋማት እና ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ፥ መድሃኒቶች እና የንጽህና መጠበቂያን ወደተጎዳው ሆስፒታል ለማድረስ ጉዞ መጀመሩን መናገራቸውን ከዞኑ ኮሚኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
+4
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share
Exit mobile version