አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም ጀመረ።
በመድረኩም የተለያዩ የሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማትን በመቶ ቀናት የተከናወኑ ተግባራት በተመለከተ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ካቢኔውም በቀረበው ሪፖርት ላይና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች በሰፊው ተወያይቷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በመድረኩ ላይ ፥ የሚከናወኑ ተግባር በክልሉ የሚታዩ ቁልፍ ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በተለይም ለረጅም ጊዜ ያልተፈቱ ጥያቄዎችን ትኩረት በማድረግ ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ተግባራት ማከናወን አስፈላጊ ስለመሆኑ አንስተዋል።
ገቢን ከመሰብሰብ አንፃር የክልሉን ገቢ አሟጦ በመጠቀም እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ እንደ ገንዘብና ኢኮኖሚ ያሉ ቢሮዎች ሌሎች ተቋማትን መደገፍና የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እንዲጎለብት መስራት ይገባል ብለዋል።
በክልሉ የእሁድ ገበያ መጀመር እንዲቻል የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ፤ ኢንቨስተሮች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች መመለስ እና በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ወደ ስራ ባልገቡ ባለሃብቶች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ዋጋ ማረጋጋትን በተመለከተም የአቅርቦት ችግር ከመቅረፍ ባለፈ በስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችና ሌሎች ህገወጥ ተግባራትን መቅረፍ እንደሚገባም አመላክተዋል።
ከሙስናና ብልሹ አሰራሮች ጋር በተያያዘም በተለያዩ ዘርፎች እየተስተዋሉ የሚገኙ ችግሮችን ለመከላከል በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንደሚገባ ጠቁመው፥ በተለይ በትራንስፖርት ዘርፉ እየታዩ ያሉ ህገወጥ አሰራሮችን ከመከላከልና ህግን ከማስከበር አንፃር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራ ማሳሰባቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

0
People reached
79
Engagements
Boost post
71
8 Shares
Like
Comment
Share
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share