Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሶማሌ ክልል በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሶማሌ ክልል በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የተመራውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎችን በጽ/ቤታቸው የተቀብሉ ሲሆን ፥ አስተዳደሩ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ በአሁኑ ወቅት ለህብረተሰባችን አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ልዑክ የ10 ሚሊየን ብር ድጋፉን ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኡስማንና ሌሎች የክልሉ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት አስረክበዋል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
በክልሉ በተከሰተው ድርቅ በህዝቡና በእንስሳት ህይወት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደረስ፣ የክልሉ መንግስት ባለው የፋይናንስ ምንጮች ሁሉ በመጠቀምና ሰብዓዊ ዕርዳታውን የበለጠ ለማጠናከር በሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ደረጃም የተለያዩ ኮሚቴዎች አዋቅሮ የተጠናከረ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version