Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ የተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ዜጎች አስቸኳይ ድጋፍ አቅርቦትን አስመልክቶ በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡
 
ርዕስ መሰተዳድሩ ፥ በክልሉ የተከሰተውን የድርቅ ሁኔታ አስመልክቶ በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ በጂያንፍራንኮ ሮቲግሊያኖና ለስራ ባልደረቦቻቸው ገለፃ አድርገዋል፡፡
 
በሶማሌ ክልል ድርጅቱ እና ሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች ድርቁን ለመቋቋም የበኩላችንን ለመወጣት እንሰራለን ነው ያሉት ተወካዩ።
 
አቶ ሙሰጠፌ መሃመድ በበኩላቸዉ ፥ እንደ መንግስት በክልሉ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች አፋጣኝ እርዳታ ለማድረስ የሶማሌ ክልል ካቢኔ አባላት ድጋፍ ማድረጋቸዉን በማስታወስ አሁንም ድርቁን ለመቋቋም ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰራን ነው ብለዋል።
 
በውይይቱ ማጠቃለያም የዜጎችን ህይወት ለመታደግ፣ በድርቁ ወቅት የሚደርሰውን የምግብ እጥረት መከላከል እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በድርቅ በተከሰቱ አካባቢዎች በአመራሮች ክትትል እየተደረገበት እንደሚገኝ ተጠቅሷል።
 
በመጨረሻም በክልሉ ዘጠኝ ዞኖች ስር የሚገኙ ከ80 በላይ ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎች በድርቁ የተጎዱ ሲሆን ፥ መንግስት የውሃ ማጓጓዣና የምግብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version