Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ ለ107 ኢንተርፕራይዞች ከ1 ሺህ 600 በላይ ካሬ መሬት የመስሪያ ቦታ ርክክብ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለ107 ኢንተርፕራይዞች ከ1 ሺህ 600 በላይ ካሬ መሬት የመስሪያ ቦታ ርክክብ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎት፣ በከተማ ግብርና እና በንግድ ዘርፍ ተሰማርተው የመስሪያ ቦታ ሲጠባበቁ ለነበሩ 107 ኢንተርፕራይዞች ነው 1 ሺህ 618 ካሬ መሬት ያስረከበው።

ርክክብ የተደረገው መሬት ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ተይዞ የነበረ እና በተደረገ የማጣራት ስራ ወደ መሬት ባንክ የተመለሰ መሆኑን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version