አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩትን ውይይት አጠናቀዋል፡፡
የዋና ፅህፈት ቤቱ ሰራተኞች በዘላቂ ድል ወደ ብልጽግና፤ የድህረ ጦርነት መዛነፎችና እርምቶች በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ነው ለሁለት ቀናት የተወያዩት፡፡
በዚህም በኢትዮጵያውያን አሸናፊነት የተጠናቀቀው የዘመቻ ኅብረ ብሄራዊ አንድነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በሌሎች ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ድሎች በሚጠናከርባቸው አቅጣጫዎች ላይ መክረዋል፡፡
በጦርነቱ የተጎዳውን ሀገራዊ ኢኮኖሚ የማነቃነቅና በወራሪው ሃይል የከፋ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ መገንባት ሌላው ሀገራዊ ድል የምናስመዘግብበት የዘመቻ ምዕራፍ መሆን አለበት ብለዋል፡፡
አሸባሪውን ሃይል በመዋጋት የታየው ሀገራዊ አንድነት በሌሎች ብሄራዊ አጀንዳዎችም መደገም እንደሚገባው ነው ተወያዮቹ ያነሱት፡፡
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የዘርፍ ሃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ÷ አካታችና አሳታፊ ሀገራዊ የምክክር መድረክ በማካሄድ በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ መግባባት ላይ ለመድረስ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በውይይቱ ከዘመቻ ህብረ ብሄራዊ አንድነት ድሎች በኋላ በሀገር ደረጃ እየተወሰዱ ያሉ ውሳኔዎችና እርምጃዎች ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅምን ታሳቢ ያደረጉ፣ የተመዘገቡ ድሎቻችንን የሚያጎለብቱና በተለይ ከምዕራቡ አለም የሚደርስብንን ያልተገባ ጫና የሚያለዝቡ መሆናቸውም ተነስቷል፡፡
ይህን ለመፈፀም የሚያስችሉ ተጨባጭ እርምጃዎችም በመንግስት በኩል እየተወሰዱ መሆኑን መጥቀሳቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

