አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ጅቡቲ የባቡር መስመር እ.አ.አ በ2021 ቀደም ካለው ዓመት ከነበረው ገቢ የ37 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ማስመዝገቡ ተገለጸ።
በዓመቱ 86 ነጥብ 13 ሚሊየን ዶላር ገቢ አግኝቷልም ነው የተባለው።
በዓመቱ በርካታ መንገደኞችንና 77 ሺህ 357 ኮንቴነሮችን ያጓጓዘው መስመሩ፥ በጅቡቲ ዶራሌህ ወደብ ላይ የጭነት ባቡር የማስተናገጃ ጊዜ ከሦስት ቀናት ወደ አንድ ቀን ተኩል መቀነሱ ተገልጿል፡፡
በሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ ያለውን የሥራ ቅልጥፍና በማሻሻል የመጫኛ እና የማውረጃ ጊዜ ከ12 ወደ ሰባት ሰዓታት ቀንሷልም ተብሏል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2021 ምንም አይነት አደጋ ባለማስመዝገብ ደህንነቱን ማስጠበቅ መቻሉንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የባቡር መስመሩ የሚያልፍበት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የባቡር ደህንነት ጥበቃ ደንብን እ.አ.አ ነሃሴ 25 ቀን 2021 ተግባራዊ ማድረጉ ተመላክቷል፡፡
የባቡር መንገዱ ማዳበሪያና ስንዴ ያጓጓዘ ሲሆን፥ የምግብ ዘይት፣ አነስተኛ መኪኖች እና የቀዘቀዙ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በማመላለስ አዳዲስ ገበያዎችን ለመፍጠር አላማ ያደረገ ስራ መስራቱም ነው የተገለፀው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

