አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ዋና ዳይሬክተር ተስፋሁን ጎበዛይ ከተባበሩት መንግስታት የፍልሰተኞች ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ሞሃመድ አብዲከር ጋር መክረዋል፡፡
በሁለቱ ተቋማት መካከል ትብብርን ማጠናከር በሚያስችሉ ተግባራት ላይ መምከራቸውን የተባበሩት መንግስታት የፍልሰተኞች ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ሞሀመድ አብዲከር በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
ዳይሬክተሩ ስደተኞችና ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

