Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል የአካባቢ ጥበቃ እና የተፋሰስ ልማት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ለምርትና ምርታማነት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የአካባቢ ጥበቃ ስራ ተጀምሯል፡፡

በክልሉ በምዕራብ አርሲ ዞን የ2014 ዓ.ም የተፋሰስ ልማት ስራዎች ዛሬ በሲራሮ ወረዳ የተጀመረ ሲሆን፥ የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር አብዱላሂ ቤካ፥ በዞኑ 13 ወረዳዎች 324 ተፋሰሶች ላይ የተፋሰስ ልማት ስራው እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በተፋሰሶች ላይ በሚከናወኑ ስራዎችም 162 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚለማ ነው ዶከተር አብዱላሂ የገለፁት፡፡

በልማት ስራው የተያዘው እቅድ እንዲሳካም ለእያንዳንዱ ተፋሰስ ሙሉ መረጃ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን ነዉ ያመላከቱት።

በክልሉ ለ60 ቀናት ለሚቆየው የአካባቢ ጥበቃ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት የሚሸፍን 6 ሺህ 448 ተፋሰሶች ለዘንድረው የአካባቢ ጥበቃ ስራ ተለይተዋል።

በቢቂላ ቱፋ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version