Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕድን ሚኒስቴር ከስምንት የከሰል ድንጋይ አውጪ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር ከስምንት የከሰል ድንጋይ አውጪ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ።
ሚኒስቴሩ 6 ቢሊየን ብር ካፒታል ካላቸው 8 የድንጋይ ከሰል አውጪ ኩባንያዎች ጋር ነው ስምምነቱን የተፈራረመው፡፡
ኩባንያዎቹ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን የከሰል ድንጋይ ሙሉ ለሙሉ ያስቀራሉ ነው የተባለው።
በስምምነቱ ወቅት የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ ስምምነቱ በሃገር ውስጥ ባለሃብት ላይ ተስፋ የተጣለ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ኩባንያዎቹ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምርት ማምረት ጀምረው ከውጭ የሚገባውን የከሰል ድንጋይ በሃገር ውስጥ ምርት መተካት እንደሚገባቸውም አቅጣጫ ሰጥዋል።
ኩባንያዎቹ የማዕድን ማውጣት እና ፋብሪካ የመትከያ የፍቃድ ምስክር ወረቀት ወስደዋል።
ፍቃድ ያገኙት ስምንቱ ፋብሪካዎች ጥናት የማድረግና ማሽኖችን የመትከል ስራዎችን አጠናቀው በተያዘው አመት ወደ ስራ በመግባት ሃገሪቱን ከውጭ ምንዛሬ እንደሚታደጉ አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ ኩባንያዎቹ ፕሮጀክቶቹ ሀገራዊ መሆናቸውን ተገንዝበው በተቀመጠለት ጊዜ እንደሚያጠናቅቁ ተስፋ አለኝ ብለዋል።
ለውጤታማነቱም ሁሉንም ድጋፍ እናደርጋለን ነው ያሉት።

በቆንጂት ዘውዴ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version