አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ”የዳያስፖራው ሚና በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ” በሚል ርእስ በአዲስ አበባ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍም የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተነስቷል።
መርሃ ግብሩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ማዘጋጀታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ከመንግስትና ከግሉ ዘርፍ ጋር በመሆን ሀገራቸውን በሚችሉት ሁሉ ለመደገፍ የሚያስችልና በዘርፉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ለመምከር መድረክ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የኢኖቬሽንና ምርምር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ ፥ ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ለማሸጋገር የዳያስፖራ ፣ የግል ባለሀብቶችና ተመራማሪዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት በምርምር እና ልማት፣ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማሳለጥ በርካታ ሪፎርሞችን እያደረገ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ዳያስፖራው በዘርፉ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
የአይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ፥ ዳያስፖራው በሚኖርበት ሀገር ለኢትዮጵያ ያደረገውን ታሪክ የማይረሳው ተጋድሎ፤ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍም እንዲደግመው ጠይቀዋል።
ዳያስፖራውን ከመንግስትና ከግሉ ዘርፍ ጋር በማገናኘት በዘርፉ በኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ለማድረግና ሀገራቸውን በሙያቸው እንዲያግዙ ማድረግ የሚያስችል የዳያስፖራ ፎረምም ተመስርቷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

